አንድምታ ትርጓሜ (Andimta)

 

አንድምታ ትርጓሜ (Andimta) ከ100 በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአንድምታ ትርጓሜ መጻሕፍትን በአንድ ላይ የያዘ ግዙፍ መተግበርያ ነው ። አፕሊኬሽኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በተለያየ ዘመናት በአንድምታ የተረጎሟቸውን የብሉይና የአዲስ ኪዳን ፣ የሊቃውንትና የሥርዓት መጻሕፍትን የያዘ ሲሆን ለአጠቃቀም ምቹ ሆኖ ተዘጋጅቶልዎታል ።

በአፕሊኬሽኑ ውስጥ የተካተቱ መጻሕፍት

በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ በቤተ ክርስቲያኗ የጉባኤ ቤት መሠረት በጥቅሉ አራቱ የመጻሕፍት ጉባኤያት የተካተቱ ሲሆን እነዚህም 
፩ ብሉይ ኪዳን
፪ ሐዲስ ኪዳን
፫ መጽሐፈ መነኮሳት
፬ መጻሕፍተ ሊቃውንት ናቸው ። 

በአሁኑ ጊዜ እነዚህን መጻሕፍት በሕትመት ማግኘት አጅግ አስቸጋሪ በሲሆን ቢገኙም እንኳን በጣም በተጋነነ ውድ ዋጋ ያስከፍላሉ ። በአጠቃላይ በአፕሊኬሽኑ ውስጥ የተካተቱ መጻሕፍትን በሙሉ ለማግኘት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ብርን ይጠይቃል ። የቤተ ክርስቲያኗ መምህራንና ምዕመናን እነዚህን መጻሕፍት በቀላሉ ሊያገኟቸው ባለመቻላቸው ችግሩን ቢያንስ በከፊል ለመቅረፍ በዚህ መተግበርያ መልክ ለማዘጋጀት ወስነናል ። 

 

በአጠቃላይ በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱ መጻሕፍትን ዝርዝር በሚከተለው መልክ አቅርበናል ። 

የብሉይ ኪዳን የትርጓሜ መጻሕፍት ዝርዝር

ኦሪት ዘፍጥረት
ኦሪት ዘፀአት
ኦሪት ዘሌዋውያን
ኦሪት ዘኍልቍ
ኦሪት ዘዳግም
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ
መጽሐፈ መሳፍንት
መጽሐፈ ሩት
መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ
መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ (ለጊዜው ያልተካተተ)
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ (ለጊዜው ያልተካተተ)
መጽሐፈ ዕዝራ
መጽሐፈ ነህምያ
መጽሐፈ አስቴር
መጽሐፈ ኢዮብ
መዝሙረ ዳዊት
መጽሐፈ ምሳሌ
መጽሐፈ ተግሣጽ
መጽሐፈ መክብብ
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን
ትንቢተ ኢሳይያስ
ትንቢተ ኤርምያስ
ሰቈቃወ ኤርምያስ
ትንቢተ ሕዝቅኤል
ትንቢተ ዳንኤል
ትንቢተ ሆሴዕ
ትንቢተ ዓሞጽ
ትንቢተ ሚክያስ
ትንቢተ ኢዩኤል
ትንቢተ አብድዩ
ትንቢተ ዮናስ
ትንቢተ ናሆም
ትንቢተ ዕንባቆም
ትንቢተ ሶፎንያስ
ትንቢተ ሐጌ
ትንቢተ ዘካርያስ
ትንቢተ ሚልክያስ

የብሉይ ኪዳን ሁለተኛ የቀኖና መጻሕፍት የትርጓሜ መጻሕፍት

መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል
መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ
መጽሐፈ ጦቢት
መጽሐፈ ዮዲት
መጽሐፈ አስቴር
መጽሐፈ ሲራክ
ተረፈ ኤርሚያስ
መጽሐፈ ባሮክ
መጽሐፈ ጥበብ
መጽሐፈ ኩፋሌ
መጽሐፈ ሔኖክ

የአዲስ ኪዳን የትርጓሜ መጻሕፍት

የማቴዎስ ወንጌል
የማርቆስ ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል
የዮሐንስ ወንጌል
የሐዋርያት ሥራ
ወደሮሜ ሰዎች
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች
ወደ ገላትያ ሰዎች
ወደ ኤፌሶን ሰዎች
ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች
ወደ ቆላስይስ ሰዎች
1ኛ ወደተሰሎንቄ ሰዎች
2ኛ ወደተሰሎንቄ ሰዎች
1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ
ወደ ቲቶ
ወደ ፊልሞና
ወደ ዕብራውያን
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት
2ኛ የጴጥሮስ መልእክት
1ኛ የዮሐንስ መልእክት
2ኛ የዮሐንስ መልእክት
3ኛ የዮሐንስ መልእክት
የያዕቆብ መልእክት
የይሁዳ መልእክት
የዮሐንስ ራእይ

መጽሐፈ መነኮሳት ፫ቱ። እነዚህም፦

፩ ማር ይስሐቅ
፪ ፊልክስዩስ
፫ አረጋዊ መንፈሳዊ

መጽሐፈ ሊቃውንት ፯ቱ። እነዚህም፦

፩ ሃይማኖተ አበው
፪ ድርሳነ ቄርሎስ
፫ ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ
፬ ተግሣጸ ዮሐንስ አፈወርቅ
፭ ፍትሐ ነገሥት
፮ 14ቱ መጽሐፈ ቅዳሴ

፩. ሥርዓተ ቅዳሴ
፪. ቅዳሴ ዘሐዋርያት
፫. ቅዳሴ እግዚእ
፬. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ
፭. ቅዳሴ ማርያም
፮. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
፯. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ
፰. ቅዳሴ ባስልዮስ
፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ
፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ
፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ
፲፭. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ

፯ አቡሻህር (ለጊዜው ያልተካተተ)
፰. ውዳሴ ማርያም

ሌሎች የትርጓሜ መጻሕፍት

ትምህርተ ኅቡአት
መጽሐፈ ኪዳን
ሊጦን ወመስተብቁዓት