Description
መዓዛ ቅዱሳን (Meaza Kidusan)
መዓዛ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚዘከሩ የቅዱሳንን ገድልና ድርሳን እንዲሁም በተለያዩ ሊቃውንት የተዘጋጁ ከ250 በላይ መልክዐ ጉባኤን በአንድ ላይ የያዘ መተግበርያ ነው።
መዓዛ ቅዱሳን ምን ይዟል?
1. ከ100 በላይ ገድላትንና ድርሳናትን በግእዝና በአማርኛ
2. ከ250 መልኮችን በግእዝና በአማርኛ
2. ከ250 መልኮችን በግእዝና በአማርኛ
ይህ አፕሊኬሽን ሦስት ክፍሎች አሉት።
ድርሳናት፤
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራ፣ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ክብርና ጸጋ፣ ስለ ቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት እና ስለ ዕለተ ሰንበት ክብር የሚናገሩ መጻሕፍት የተካተቱበት ክፍል ነው።
ገድላት ፤
በሕይወታቸው እግዚአብሔርን ያከበሩ ቅዱሳን ሰዎች ያለፉበትን የመከራ ሕይወትና በክርስትናቸው ምክንያት ያገኛቸውን ፈተና ያለፉበትን ወንጌላዊ ጥበብ የሚተርክ፤ ለአማኒያን መማሪያ ለቅዱሳን መዘከሪያ ኾነው የሚቀርቡ አዋልድ ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው። የገድል መጻሕፍት ጻድቃን፣ ሰማዕታት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ትእዛዘ እግዚአብሔር እንዲከበር ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን እንዲጠበቅ ከአላውያን ነገሥታት፣ ከቢጽ ሐሳውያን፣ ከጠላት ዲያብሎስና ከፈቃደ ሥጋ ጋር ያደረጉትን ተጋድሎ የሚያወሱ መጻሕፍት የተካተቱበት ክፍል ነው፡፡
መልክዐ ጉባኤ፤
የባለመልኮቹን መልክ ከስማቸው በመጀመር ከራስ ፀጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ድረስ በቅደም ተከተል በስንኝ (በአርኬዎች) የሚያመሰግኑ ገላጭ ግጥሞች ናቸው። እነዚህም መልኮች በሥርዓተ ማኅሌትና በተለያዩ የቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ የሚውሉ ናቸው።
ይህን አፕሊኬሽን በመጠቀም የቅዱሳኑን ሕይወትና ተጋድሎ ይማሩበት ፣ ከተሰጣቸው በረከት ይካፈሉ።
ይህን አፕሊኬሽን በመጠቀም የቅዱሳኑን ሕይወትና ተጋድሎ ይማሩበት ፣ ከተሰጣቸው በረከት ይካፈሉ።
‘
Download Links
Apple Appstore https://apps.apple.com/app/id6479744687
Direct Download https://biranapps.com/download/meazakidusan/

Reviews
There are no reviews yet.