Metsihafe Kidase መጽሐፈ ቅዳሴ

(1 customer review)

50.00 Br

Category: Tags: , ,

Description

ቅዳሴ

በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡  ከጸሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡ ፩. የቁርባን መስዋዕት፤ በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡ ፪. የከንፈር መስዋዕት፤ ካህኑ፣ ዲያቆኑና ሕዝቡ በመቀባበል በአንድነት ምስጋና ለፈጣሪያቸው የሚያቀርቡበት የከንፈራችን ፍሬ የሚሰዋበት የፀሎት ክፍል ፀሎተ ቅዳሴ ነው፡፡ ፫. የመብራት መስዋዕት፤ በቅዳሴ ጊዜ የሚበራው ጦፍ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የሚሰጥ የመብራት መስዋዕት ነው፡፡ ምሳሌነቱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው ይህውም ጌታችን ጨላመ ለሆነ ዓለም ብርሃን ሆኖ ብርሃንን ሊያበራ ወደ ዓለም መቷልና ነው፡፡ ፬. የዕጣን መስዋዕት፤ የዕጣን ፀሎት ካህኑ ብቻ የሚያጥነው ሲሆን ይህውም በማዕጠንቱ አማካኝነት ቅዱሱን እጣን በመንበሩ፣ በቅዱሳን ስዕላቱ፣ በሕዝቡ መካከል ያጥናል ይህውም የሕዝቡን ፀሎት ወደላይ በደሥላሴ መንበር ይዞ ይወጣል በሰማይም ያሉ ቅዱሳን መላእክት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ የሥላሴን መንበር እንደሚያጥኑ ሁሉ በምድርም ያለው ካህን የሰማያዊው ምሳሌ ነውና በምድር ያውን መንበር በማጠን ለእግዚአብሔር የዕጣን መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ፭. የሰውነት መስዋዕትነት፤ በቅዳሴ ጊዜ አብዛኛውን ሰዓት ሙሉውን ማለት ይቻላል በመቆም የሚፀለይ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በመሐል 2 ጊዜያት ብቻ የስገዱ ትዕዛዝ ሲተላለፍ ሕዝቡ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪው አዞሮ እራሱን አዋርዶ ይሰግዳል በእግዚአብሔር ፊት መቆምም ሆነ መስገድ ለእግዚአብሔር የሚሰጥ የሰውነት መሥዋዕት ነው፡፡ ይህ የፀሎት ክፍል (ቅዳሴ) በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል። ፩. የዝግጅት ክፍል ፪. የንባብና የትምህርት ክፍል ፫. ፍሬ ቅዳሴ እዚህ ፍሬ ቅዳሴያት እንደየበዓሉ ይለዋወጣተሉ ብዛታቸውም ፲፬ ናቸው። እነዚህም፤ ፫.፩. ቅዳሴ ዘሐዋርያት ፫.፪. ቅዳሴ እግዚእ ፫.፫. ቅዳሴ ዘዮሐንስ ወልደ ነጓድጓድ ፫.፬. ቅዳሴ ማርያም ፫.፭. ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት ፫.፮. ቅዳሴ ዘአትናቴዎስ ፫.፯. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ፫.፰. ቅዳሴ ባስልዮስ ፫.፱. ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ ፫.፲. ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ ፫.፲፩. ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ፫.፲፪. ቅዳሴ ዘቄርሎስ ፫.፲፫. ቅዳሴ ዘያዕቆብ ዘሥሩግ ፫.፲፬. ቅዳሴ ዘዲዮስቆሮስ ቅዳሴ የምስጋና ሁሉ መደምደሚያ (ማሰሪያ) በመሆኑ እያንዳንዳችን በቤተክርስቲያን ተገኝተን የጸሎቱ ተሳታፊ በመሆን ለእኛ ኃጢአት በቀራንዮ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሥጋውና ደሙን ልንቀበልና የክብሩ ወራሾች ልንሆን ይገባል።  ሥጋውና ደሙ የሚፈተተው ለሕጻናትና ሽማግሎች ብቻ ሳይሆን ከ40 እና ከ80 ቀን ጀምሮ ከመንፈስ ቅዱስ ልጅነት ላገኙ በሁሉም እድሜ ክልል ላሉ ነው። ስለዚህ ለሠራነው ኃጢአት ንስሐ እየገባን ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ጸሎተ ቅዳሴው ከመጀምሩ በፊት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት በሥርዐተ ቅዳሴው እና በፍሬ ቅዳሴው የሚነበቡትን ምስጢራት ልናስተውል ልንረዳ ይገባል።  በምናስቀድስበትም ጊዜ ከመሰቀሉ በፊት በዕለተ ሓሙስ የሠራልንን ሥርዐት እንዲሁም ለእኛ ለሰው ልጆች በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ ተሰቅሎ ሥጋውን የቆረሰልን፣ ደሙን ያፈሰ ሰልንን መሆኑን እያሰብን የሠራነውንም ኃጢአት እንዲያስተሰርይልን ሊሆን ይገባል። ይህ መተግበሪያ እነዚህን የቅዳሴ ክፍሎች በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የያዘ ሲሆን የተወሰኑ ክፍሎችንም በትግርኛ አካቷል።

 

Price: 50ETB (3.99 USD)

 

1 review for Metsihafe Kidase መጽሐፈ ቅዳሴ

  1. gechadmin

    cool

Add a review

Your email address will not be published. Required fields are marked *